+251944477598 admin@marekospecialweredasito.gov.et

ዜና

የተለጠፉ ዜናዎችን እያዩ

የማረቆ ልዩ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን ቅድመዝግጅት ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ
April 03, 2026

የማረቆ ልዩ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን ቅድመዝግጅት ስራዎች ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ


‎       ማረቆ /ቆሼ 23/07/2018 ዓ/ም
‎          ====================
‎የማረቆ ልዩ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የ2018 ዓ/ም የፈጠራ ስራዎች ኤግዚብሽን አውደርእይ ቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ገመገመ። አራቱ ባለድርሻ ተቋማት( ሳኢቴ ጽ/ቤት፣ ት/ት ጽ/ቤት፣ቴ/ሙያ ጽ/ቤት፣ ኢንተርፕራይዝ ጽ/ቤት) የእስካሁን የዝግጅት ምዕራፍን የገመገመ ስሆን ለኤግዚብሽኑ የሚያስፈልጉ አጠቃላይ መርሀግብር በኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲመራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
‎በውይይቱ የአረቱም ተቋማት ኃላፊዎች ተገኝተው የጋራ የማስፈጸሚያ  ዕቅድ ላይ በጥልቀት ተወያይተው በአጭር ጊዜ ውስጥ ለክልል ብሎም ለሀገር ችግር ፈቺ የፈጠራ ስራዎችን ይዞ ለመቅረብ በሚያስችል መልኩ ዝግጅት መደረግ አለበት በሚል አቋም ተይዞ ውይይቱ ተጠናቋል።

ወደ ዜናዎች ተመለስ